የማዕከላዊ እዝ ከፍተኛ ሃላፊዎች የሰራዊት ክህደት እየጨመረ መሄዱ ስላሳሰባቸው የእያንዳንዱን ወታደር ንብረት እየፈተሹ በርካታ ወታደሮችን ማሰራቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ፣ በምንጮቻችን መረጃ መሰረት የማዕከላዊ እዝ አመራሮች በየዕለቱ የሚከዳው የሰራዊት ቁጥር ስላሳሰባቸው ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓ/ም የእያንዳንዱን ወታደር የግል ንብረት ሲፈትሹ የዋሉ ሲሆን በፍተሻውም ከ180 በላይ የሚሆኑት የሲቪል መታወቂያ ካርድ ያላቸው ወታደሮች መገኘታቸውን አስረድቷል። […]
