ብዙ የወርቅ ክምችት አለበት በተባለው አኮቴ ተጨማሪ መሬት ንብረትነቱ ለሼክ መሃመድ አል-አሙዲን ለሆነው ሜድሮክና የህወሃት ንብረት ለሆነው ኤፈርት መሰጠቱ ህዝባዊ ቁጣ ቀስቅሷል። ሚድሮክ ኩባንያ በሻኪሶ ለገደምቢ ከ20 አመታት በላይ የወርቅ ማዕድን ቢያወጣም የአካባቢው ህብረተሰብ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ አለመሆኑ ቁጭት እንደፈጠረበት ተመልክቷል። ሚድሮክ በየአመቱ 4.5 ሜትሪክ ቶን ወይም 4500 ኪሎግራም ወርቅ ሲያወጣ ቢቆይም የነዋሪው የዕለት ተዕለት ህይወት […]
