በምዕራብ አርሲ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ወደ ሌሎች አጎራባች ቀበሌዎች መዛመቱንና በአካባቢው ከፍተኛ ግጭት በመካሄድ ላይ መሆኑን እማኞችን ዋቢ በማድረግ አዲስ ስታንዳርድ መጽሄት ማክሰኞ ዘግቧል። ይኸው ተቃውሞ በሻላ፣ ሲራሮ፣ አጄና፣ ሻሸመኔ ከተማ ተዛምቶ የሚገኝ ሲሆን፣ የፀጥታ ሃይሎችም ከነዋሪዎች ጋር ግብግብ ውስጥ መሆናቸውን መጽሄቱ ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ አቅርቧል። የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በወሰዱት የተኩስ እርምጃዎች በሻሸመኔ ከተማና በአቅራቢያዋ ባሉ […]
