የዛሬዋ ኢትዮ ምህዳር ስለ ተቃዋሚዎች ውህደትና ህብረት ሰፊ ሀተታ ይዛ ወጥታለች፡፡ በተለይ ዶክተር ሀይሉ አራዕያ ስለ ተቃዋሚዎች ውህደት ያነሱት ሀሳብ ወቅታዊና አንገብጋቢ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ ዶክተር ሀይሉ የተቃዋሚዎችን ድክመት በድፍረት ጽፈዋል፡፡ ዶክተሩ ተቃዋሚዎች ካልተዋሃዱ፣ ካልተባበሩ በስተቀር ምርጫ ሊያሸንፉና ለውጥ ሊያመጡ እንደማይችሉ አስረግጠው ነግረዋቸዋል፡፡ ዶክተሩ የሚሉት ለስልጣን ሳይሆን ለህዝብ ተዋሃዱ፣ ካለፈው ስህተት፣ ከሌሎች አገራትም ተማሩ፣ ህዝብን አታስገዙ፣ […]
