ወሎን ሰፈር ተሻግሮ ሩዋንዳ ሙልሙል ዳቦ አካባቢ ወደ ቦሌ በሚወስደዉ መንገድ በስተቀኝ ወደ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ይገኛል ከዩኒቨርሲቲዉ በተጓዳኙ በስተግራ ካለዉ ነጭ ህንጻ ላይ በደረጃ ቀስ እያልን ወደ 5ተና ፎቅ አመራን ከቢሮዉ በተያያዘ ቱሪዝም ኤጀንሲ ባጎራባች ሲኖር ከስሩ ደግሞ ሱፐር ማርኬት አለ በዋናነት ወደዛ የሄድንበት ምክንያት የበረከት ስሟን ቢሮ እዚያ እንደሚገኝ በደረሰን መረጃ መሰረት ነዉ። […]
