መደፈር፣ ያሉበት ሥፍራ አለመታወቅ ብሎም መገደል ለማዕከላዊቷ አፍሪካ ሪፐብሊክ ዜጐች የተለመደ ከሆነ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ንፁኃን እያለቁ ናቸው፡፡ ገዳዮች ደግሞ ከዕለት ዕለት ኃይል እያገኙ ነው፡፡ ሸማቂዎች በነገሡባት ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ በሃይማኖት ተከፋፍለው የሚጨፋጨፉት ወገኖች፣ በተለይ ለንፁኃን ሕፃናትና ሴቶች ጦስ ሆነዋል፡፡ በአገሪቱ ምግብ ማግኘትም ከብዷል፡፡ የሚጠጣ ውኃም እንዲሁ፡፡ ቤት ውስጥ አድሮ አንገትን ለሰይፍ ከመስጠት […]
