ድምፃዊ ጎሳዬ “ሃይማኖቱን ቀየረ” በሚል በመገናኛ ብዙሃንና በድረ-ገፆች የተሰራጨው መረጃ ሀሰት መሆኑን ገልፆ መገናኛ ብዙሃኑ ስህተታቸውን ካላስተባበሉ ክስ እንደሚመሰርት በጠበቃው በኩል ለአዲስ አድማስ ገለፀ፡፡ ድምፃዊ ጎሳዬ ተስፋዬ “ሃይማኖቱን ቀይሮ ሙዚቃ በቃኝ በማለት መዝሙር ሊያወጣ ነው” በሚል በዛሚ ኤፍ ኤም ሬዲዮና በ “ቃልኪዳን” መጽሔት የተሰራጨው ሃሰተኛ ዘገባ የድምፃዊውን ስምና ዝና የሚያጠፋ ነው ያሉት ጠበቃው አቶ ጳውሎስ ተሰማ፤ […]
