ባለፉት ወራቶች ቴዎድሮስ ካሳሁን ወይም “ቴዲ አፍሮ” ከኮካ ኮላ እና በስፋት ሲወራ ከከረመው የዓለም ዋንጫ የኢትዮጵያው ቅጂ ሙዚቃ ጋር ስለነበረው ግንኙነት ያለንን አቋም እንድንገልፅ በሚጎርፍልን ጥያቄዎች ምክኒያት ከፍተኛ ጫና ስደረግብን ቆይተናል፡፡ በበኩላችን በተገባው የውል ስምምነት ላይ የግንኙነቱን ሚስጥራዊነት ለመጠበቅ ቃል ኪዳን የገባን እና ማክበር የነበረብን ቢሆንም ቅሉ የቴዲ አፍሮ እና የኮካ ግንኙነት ወሬ እንዴት አፈትልኮ […]
