ሰላማዊት ከበደ (ስሟ ተቀይሯል)፡፡ በሁለት ዓይነት የፍቅር ግንኙነት ውስጥ ትገኛለች፡፡ ቤት ተከራይቶ ያስቀመጣትና የሚረዳት የውጭ ዜጋ ወጣት አለ፡፡ በሌላ በኩል አፈቅረዋለሁ የምትለው ሌላ ኢትዮጵያዊ ጓደኛም አላት፡፡ ዕድሜዋ አሥራ ዘጠኝ እንደሆነ፤ ከፍቅረኛዋ ጋር ከሦስት ዓመት በላይ አብረው መቆየታቸውን ትናገራለች፡፡ እሷ እንደምትለው ከውጭ ዜጋው ወዳጇ ጋር ከተገናኙ ከአንድ ዓመት በላይ ሆኗል፡፡ ታላቅ እህቷ የውጭ ዜጋ ወዳጅ ነበራት፡፡ […]
