የአሸባሪነት ታፔላ ለጥፎ ብሎገሮችንና ጋዜጠኞችን አሳዶ በማሰርና በማሰቃየት ነፃ ሚዲያን ከአገሪትዋ ለማጥፋት እየሰራ ያለው የወያኔ መንግስት በእኩይ ተግባሩ በመቀጠል በትናንትናው ለት በአምስት መጽሔቶች እና አንድ ጋዜጣ ላይ ወንጀል ክስ መመስረተ። ለዚህም የሰጠው ምክንያት በህገ፡መንግስቱ የተደነገጉ ገደቦችን በመጣስ፤ ስራዬ ብለው ብሔራዊ ደህንነትን አደጋ ላይ በሚጥል መልክ አመጽና ሁከትን የሚቀሰቅሱ፤ አክራሪነትን እና ሽብርተኝነትን የሚያወድሱ እና የሚያበረታቱ አሉ፡፡ […]
