‹ኃይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው) አረፈ፡፡› ጠዋት ሰምቼው ክው አድርጎ ያስቀረኝ አሳዛኝ ዜና ነው፡፡ ምናልባት ብዙዎች በሕይወት መኖሩን አያውቁም ነበር ይሆናል፤ ስሙን ሰምተው አውቀውት፣ ‹ማነው ምን ሰራ› የሚሉም አይጠፉም፤ …እሳት የላሰ ባለቅኔና ደራሲ ነበር፡፡ በዘመኑም ግፍን ተጠይፎ በቻለው ልክ ለነፃነት ታግሏል፡፡ ምንም ሆነ ምን ግን… አበሻ ይህ ደንብ አለው፤ ሰው ፅዋው ሲሞላ ያሰባስባል፡፡ ሰው ሲሞት ያስተሳስባል፡፡ እግዚአብሔር […]
