የደህንነት ሃይሎች ዜጎችን እያፈኑ መውሰዱን ቀጥለውበታል!
ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን ተጠናክሮ የቀጠለው የገዢው ፓርቲ አፈና መንግስት ራሱ ያስታጠቃቸውን ታጣቂዎች ትጥቅ እስከማስፈታት መድረሱን ምንጮች ገለጹ በትግራይና በአማራ ክልሎች ባለፉት ሶስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው አፈና ቀጥሎ ጥቅምት 26 ቀን 2007 ኣም የሰላም ታጋይ እየጠባለ የሚታወቅ ወጣት ሽሻይ አዘናው በመቀሌ ከተማ...
View Articleየፌደራል ሚኒስቴር እና ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ለቀረበባቸው ክስ መልስ እንዲሰጡ ታዘዙ
የፌደራል ሚኒስቴር እና ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ለቀረበባቸው ክስ መልስ እንዲሰጡ ታዘዙ በ2005 ዓ.ም በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ይኖሩ የነበሩ የአማርኛ ተናጋሪዎች ላይ ህገ ወጥ የሆነ ማፈናቀል ተፈጽሞባቸዋል፣ ንብረታቸው ወድሟል በሚሉ እና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ በሰማያዊ ፓርቲና በአንድነት ፓርቲ አሳሳቢነት...
View Articleወጣቶች ለምን አክራሪ ሙስሊም አማፂ ቡድኖችን ይቀላቀላሉ
አክራሪ ሙስሊም አማፂ ቡድኖችን የሚቀላቀሉት በብዛት ወንድ ወጣቶች ሲሆኑ ፤ ከቅርብ ጊዜ አንስቶ የሴቶቹም ቁጥር እየጨመረ መጥቷል። ወጣቶች ለምን የሳላፊቾች ቡድንን እንደሚቀላቀሉ እና ያላቸውን ሚና በዛሬው የወጣቶች ዓለም እንቃኛለን።ቤተሰቦቼ «እስላማዊ ቅዱስ ጦርነትን»የሚቃወሙ ከሆነ ፤ እነሱንም ለመግደል ዝግጁ ነኝ...
View Articleእሥሩ ተጧጡፏል፣ አንድነት ምርጫ እንዳይወዳደር አገዛዙ ይፈልጋል (ግርማ ካሳ)
ዜጎች መታሰራቸው እየቀጠለ ነው። በተለይም የአንድነት ፓርቲ አባላት (በጎንደር፣ በትግራይ፣ በመቱ፣ በአዲስ አበባ ፣ በወላይታ ….) ። ብዙዎች ከፍተኛ ደብደባ እየደረሰባቸው ነው። ሕወሃት ፣ በሕዝብ እንደተጠላ ስላወቀ የአንድነት ፓርቲ እንዲዳከም ወይም ከምርጫው ዉጭ እንዲወጣ እየሰራ ነው። አንድነት ሊያሸንፈው...
View Articleፓርቲዎች ለሃይማኖት ተቋማት ጥሪ አቀረቡ
9 ተቃዋሚ ፓርቲዎች የመሰረቱት ትብብር ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› ቀደም ብለው ባሳወቁት የአንድ ወር መርሃ ግብር መሰረት የጀመሪያውን ጥሪ ለሃይማኖት ተቋማት አድርገዋል። ፓርቲዎቹ አገራችንና ህዝቧ በተፈጥሮ ሚዛን መዛባት በሚከሰትበትም ጊዜ ሆነ በአገዛዝ ሥርዓቶች ምክንያት በችግር ውስጥ በሚወድቁበት ጊዜ የኃይማኖት...
View Articleበአዲስአበባ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ በተለይ በዚህ ሳምንት ተባብሶ መቀጠሉ የአዲስአበባ ነዋሪዎችን እያበሳጨ ነው፡፡
ነዋሪዎች እንደሚሉት በተለይ ባሳለፍነው አንድ ሳምንት ጊዜያት ውስጥ መቆራረጡ በወሳኝ ሰዓታት ጭምር ማለትም በምሽት እና በጠዋቱ ጊዜያት ተጠናክሮ መቀጠሉንና በዚህ ምክንያት ለከፍተኛ ኪሳራና ወጪ እየተዳረጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ባለስልጣናት «የኃይል እጥረት የለም፣ እንዲያውም ተርፎን ለጎረቤት ሀገራት ኤክስፖርት...
View Articleአምሳሉ ገኪዳንና ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ታሰሩ
ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ የብር 20,000(የሃያ ሺህ ብር) ዋስ ተጠይቆበት ወደ ማረፍያ ክፍል መግባቱ ታወቀ፡፡ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር የጅማ ዩኒቨርሲቲ ባቀረበበት ክስ የፕሬስ ህጉን በሚፃረር መልኩ ለአራት ቀናት በማዕከላዊ ታስሮ የተለቀቀው ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ክሱ እንደ አዲስ እንዲቀሰቀስበት ከተደረገ በኋላ ዛሬ...
View Article‹ኃይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው) አረፈ፡፡
‹ኃይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው) አረፈ፡፡› ጠዋት ሰምቼው ክው አድርጎ ያስቀረኝ አሳዛኝ ዜና ነው፡፡ ምናልባት ብዙዎች በሕይወት መኖሩን አያውቁም ነበር ይሆናል፤ ስሙን ሰምተው አውቀውት፣ ‹ማነው ምን ሰራ› የሚሉም አይጠፉም፤ …እሳት የላሰ ባለቅኔና ደራሲ ነበር፡፡ በዘመኑም ግፍን ተጠይፎ በቻለው ልክ ለነፃነት ታግሏል፡፡...
View Articleበዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ የሟች ኢትዮጵያዊት ቤተሰብ ገንዘብ ተቀብለው ገዳዮች ከእስር እንዲወጡ ማድረጋቸው ተዘገበ
ኢሳት ዜና :- ገልፍ ኒውስ ባወጣው ዘገባ 4 ወንዶች አንዲት ኢትዮጵያዊትን አአስገድደው መኪና ላይ ከጫኑዋት በሁዋላ በየተራ ደጋግመው በመድፈርና በመኪናቸው ገጭተው በመግደል በላዩ ላይ ድንጋይ በማስቀመጥ ለማምለጥ ሞክረዋል። ግለሰቦቹ ተይዘው ፍርድ ቤት ከቀረቡ በሁዋላ የጄራጂ ፍርድ ቤት በግለሰቦቹ ላይ የሞት ፍርድ...
View Articleታላቅ ሕዝባዊ የውይይት መድረክ በአምስተርዳም ከተማ አበራ የማነ አብ ዶ/ር አረጋዊ በርሔ እና ዶ/ር መላኩ በሚገኙበት
የፊታችን ቅዳሜ ኖቬበር 15 ቀን 2014 ከ 14:00- ጀምሮ አድራሻ: 1e Helmersstraat 106, 1054 EG Amsterdam next to VENA office Filed under: NEWS
View Articleየፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) ልዩ አማካሪ አቶ አሰፋ ከሲቶ ተነሱ፡፡
የፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) ልዩ አማካሪ አቶ አሰፋ ከሲቶ ተነሱ፡፡ አቶ አሰፋ የተነሱት በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ፊርማ በተጻፈ ደብዳቤ ነው፡፡ በአቶ ኃይለ ማርያም ፊርማ የወጣው ደብዳቤ፣ አቶ አሰፋ ከኃላፊነት የተነሱበትን ምክንያት ያልጠቀሰ ሲሆን፣ አቶ አሰፋም በምን ምክንያት እንደተነሱ...
View Articleበፋይናንስ ችግርና በአንድነት ጉዳይ የሚፈተነው መድረክ
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ሒደት ውስጥ ብልጭ በማለት ለብዙዎች የተስፋ ስንቅ አስይዞ የነበረው ምርጫ 97 በአወዛጋቢ ሁኔታ ከተጠናቀቀ በኋላ በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ግለሰቦች የአገሪቱ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ወደኋላ እየተንሸራተተ ነው በማለት ይተቻሉ፡፡ ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ ደግሞ አገሪቱ...
View Articleአቃቢ ህግ በጦማርያኑና ጋዜጠኞቹ ላይ የመሰረተውን ክስ እንዲያሻሽል ታዘዘ •ክሱ ተሻሽሎ መቅረቡን ለማየት ለህዳር 24...
የፌደራል አቃቢ ህግ በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ በጦማርያኑና በጋዜጠኞቹ ላይ የመሰረተውን የሽብር ክስ እንዲያሻሽል የልደታ ከፍተኛ ችሎት ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ፍርድ ቤቱ ዛሬ ህዳር 3/2007 ዓ.ም በዋለው ችሎት ቀደም ብሎ የተከሳሽ ጠበቆች ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ መርምሮ ብይን በመስጠት በንባብ አሰምቷል፡፡...
View Articleየገቢዎችና ጉምሩክ ከፍተኛ ኦፊሰር ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተያዙ
የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ቃሊቲ ጉምሩክ ጽሕፈት ቤት ከፍተኛ ኦፊሰር፣ አቶ ዘመን ይሰማው 40,000 ብር ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል በሚል ተጠርጥረው ክስ ተመሠረተባቸው፡፡ የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በተጠርጣሪው ላይ የመሠረተው ክስ እንደሚያስረዳው፣ የፈረንሣይ ኤምባሲ ሠራተኛ...
View Articleተማሪዋ በተሳፈረችበት ታክሲ ታፍና ተወስዳ በደረሰባት አስገድዶ መድፈር ሕይወቷ አለፈ
ተጠርጣሪዎቹ በፖሊስ በቁጥጥር ሥር ውለዋል በአዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ቄራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ አየር ጤና አካባቢ አንዲት የአሥረኛ ክፍል ተማሪ በተሳፈረችበት ታክሲ ታፍና ከተወሰደች በኋላ በደረሰባት አስገድዶ መደፈር ጉዳት ሕይወቷ ማለፉን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ ሟቿ ተማሪ ሃና ላላንጎ ጥቅምት 21 ቀን...
View Articleአምባገነንነት ከምድረገፅ መጥፋት አለበት!
ባለፈው ሳምንት ቡርኪናፋሶን ለ27 ዓመታት እንደ ግል ንብረታቸው ሲያዙባት የከረሙት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ብሌስ ኮምፓዎሬ፤ የሥልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም ሲሉ ህገመንግስቱን ለማሻሻል ያደረጉት (ንቀትና ድፍረት የተቀላቀለበት ነው) ሙከራ ያስከተለው ውጤት ያልጠበቁት ነበር፡፡ (አመዳቸውን ቡን ሳይል አልቀረም!) ምንም...
View Articleለነፃነታችን በጋራ ቆመን ታሪካዊ ግዴታችንን የምንወጣበት ጊዜው አሁንና አሁን ነው!
የኢትዮጵያ ህዝብ ፍትህና ነፃነት እንደናፈቀ፤ ሀገራችንም ቅን መሪ እንዳጣች ዘመናት ተቆጠሩ። በየጊዜው የመጡ ገዢዎቿ በህዝቧ መሥዕዋትነትና ታላቅ ተጋድሎ በተገኘ ድል ሥልጣን ላይ ከወጡ በሗላ፤ በህዝብ ፊት ቃል የገቡትን ወደ ገደል ሰደው፤ ዘግናኝ በሆነ ሥርዓታቸው በማፈን ህዝቧን ለከፋ ድህነትና ጉስቁልና ሲዳርጉት፤...
View Articleዩጋንዳና የቀጣዩ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ዕጩ ጉዳይ
የዩጋንዳ «ናሽናል ሬዚዝተንስ ሙቭመንት» ፓርቲ ፕሬዚደንት ዮዌሪ ሙሴቬኒን እአአ ለ2016 ዓም ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በዕጩነት ለማቅረብ የያዘው ዕቅድ ብርቱ ክርክር አስነስቷል። ዮዌሪ ሙሴቬኒ እአአ ከ1986 ዓም ወዲህ በዩጋንዳ የፕሬዚደንትነቱን ሥልጣን እንደያዙ ይገኛሉ። ፕሬዚደንት ሙሴቬኒ የሀገሪቱን ሕገ መንግሥት...
View Article‹‹ከልዩነታችን ይልቅ አንድነታችን ይልቃል›› ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ከቃሊቲ
ቀጥሎ ያለው አጭር መልዕክት ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ በእስር በሚገኝበት ቃሊቲ ለተገኘው የነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር የገለጸው መልዕክቱ ነው፤ እንዲህ ቀርቧል፡፡ ‹‹ነገሮችን ማወሳሰቡ ለማናችንም አይጠቅምም፡፡ ደግሞ በማናቸውም መልኩ የተወሳሰበ ችግር በመካከላችን ያለ አይመስለኝም፤ የለምም፡፡ እኛ እንደ ሀገር እና ህዝብ...
View Articleሽመልስ ከማልና ፈትያ የሱፍ በፕሬስ ድርጅት እየተወዛገቡ ነው
‹ችግሮች በአስቸኳይ ካልተፈቱ ለበላይ አካል እናሳውቃለን›› ፈትያ የሱፍ ‹‹ችግሮቹ ውጫዊ ናቸው›› አቶ ሽመልስ ከማል በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማል እና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የባህልና ቱሪዝም ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፈትያ የሱፍ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት...
View Article