ከሁለት ሳምንት በፊት ከማዕከላዊ የምርመራ ቢሮ ከወዲያኛው ጫፍ የደወለው ሰው እንደነገረኝ ‹‹ከፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ነው›› ብሎ ደወለልኝ፡፡ ደዋዩ ቆንጆ መጽሔት መሆኑን ካጣራ በኋላ ዋና አዘጋጇ ስልክ ላይ ብደውል ዝግ ነው ፤ ጥር ወር ላይ ባወጣችሁት ዘገባ እኛ ጋ ክስ ተመስርቶባችኋል አለኝ፡፡ ስለሆነም ለዋና አዘጋጇ መልዕክት አድርሱ መጥታ ቃሏን ትስጥ አለኝ፡፡ ለጊዜው በቅርብ እንደሌለች ነገርኩት፡፡ […]
