ፓርቲዎቹ ይህን አስታወቁት ባወጡት መግለጫ ነው። ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው ደብዳቤ ለመቀበል አሻፈረን ሲል የነበረው መስተዳድሩ በፖስታ የተላከለትን ደብዳቤ ከተቀበለ በሁዋላ ከህገመንግስቱና ከአዋጁ ቁጥር 3/1983 ተቃራኒ የሆኑ ምክንያቶችን በመደርደር ለሠላማዊ ሠልፉ ዕውቅና አልሰጠሁም ሲል ህዳር 22 ቀን ድብዳቤ መጻፉን አስታውቀዋል፡፡ “በመሠረቱ መስተዳድሩ ጊዜና ቦታ እንዲቀየር አስተያየት ከማቅረብ ያለፈ ዕውቅና የመንፈግ መብት የሌለው በመሆኑ ትብብሩ የደብዳቤውን መልዕክት ያልተቀበለ […]
