የተመልካች ድርቅ የመታው ኢቲቪ ጭንቅ ውስጥ እንዳለ ማነው የሚረዳው? ጭንቀቱ ሲጀማምረው መጀሪያ ስሙን ቀየረ።መች ችግሩ ከስሙ ሆነና!በማስከተል ሎጎውን ቀየረው።የቢቢሲን ኮፒ አድርጎ አሳየን።ይህንንም ለአንድ ወር ሳይገለገልበት አሁን በሚጠቀምበት በአረንጏዴ ቀየረው።መደበኛ ዜና መግቢያው ከአፍሪካ ዋንጫ መግቢያ ተመሳሳይ ነው።እንደውም ስፖርት የሚጀምር ይመስላል።ይህም አንድ ወር መቆየቱ እንጃ! በዚህም ስላረካ እባካቹ ተመልካቾች ሎጎ ምረጡልኝ በስምንት መቶ ምናምን ቁጥር ኤስኤምኤስ አድርጉ […]
