(መልዕክት-አብዬታዊያን) ተመስገን ደሳለኝ ከዝዋይ እስር ቤት “ባለወር ተተካ ተቀበለኝ ትግሌን እንካ” (ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን) …ሲያሻው እየጋመ፤ ሲያሻው እንደበረዶ እየቀዘቀዘ በመካሄድ ላይ ያለው የፀረ-ጭቆና ትግል እንደዋዛ ግማሽ ክፍለ ዘመን አስቆጠረ፡፡ የሂደቱ ክፉ ጎን ደግሞ የአያሌ ብርቱ ወንድም-እህቶቻችንን የህይወት ግብር እየጠየቀ ዛሬ ድረስ ተጉዟል፡፡ በተለይም ሁለቱ ቀደምት አብዮቶች (የ1966ቱ እና የ1983ቱ) ብረት-ነከስ ናቸውና የትውልድ ክፍተት […]
