አርቲስት ብርሃኑ ተዘራ በቅርቡ ‹‹ወገኔ›› በሚል ያወጣውን ዜማ ሰማያዊ ፓርቲ ለቅስቀሳ እንዲጠቀምበት መፍቀዱን ለፓርቲው በላከው ደብዳቤ ገልጾአል፡፡ ኤፍ ኤም 96.3 ሰማያዊ ፓርቲ ለቅስቀሳ በላከው መልዕክት ላይ በማጀቢያነት የተጠቀመበት ሙዚቃ የባለ መብቱን ፈቃድ አላገኘም በሚል የቅስቀሳ መልዕክቱን መመለሱ ይታወሳል፡፡ በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢብኮ) የሰማያዊ ፓርቲን የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክት ‹‹እንደገና አስተካክሎ ካልላከ ለማስተላለፍ እቸገራለሁ›› በሚል መመለሱን […]
