አሸባብ በጣም መዳካሙን የሶማሊያ መንግሥትና ደጋፊዎቹ መናገር ከጀመሩ ከሁለት ዓመት በላይ ተቆጠረ።ሶማሊያ ግን የአክራሪዉ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ጥቃት ተለይቷት አያዉቅም።ሆቴሎች፤ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ፅሕፈት ቤቶች፤ አብያተ-መንግሥታት፤ መስሪያ ቤቶች፤ የጦር ሠፈሮች፤ አዉሮፕላን ማረፊያዎች፤ የመሰብሰቢያ አዳራሾች ሁሉም ይጠቃሉ፤ ሁሌም ይሸበራሉ። የሶማሊያዉ አክራሪ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን አሸባብ በደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ ትልቅ ከተማ ባይዶዎ የሚገኘዉን የዓለም አቀፍ ድርጅቶች፤የጦርና ሐይልና […]
