በተለያዩ የባለ ሥልጣናትና የእምነትመሪዎች መግለጫዎች ላይ በሊቢያ ምድር የተሠዉትን ሰማዕታት በኢትዮጵያዊነታቸው ወይም በስደተኛነታቸው ብቻ አደጋ እንደደረሰባቸውተድርጎ እየተነገረ ነው፡፡ እነዚህ ክቡራን ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ የተሠዉትም እምነታቸውን አንለውጥም ስላሉ ነው፡፡አይሲስ የሠዋቸው በኢትዮጵያዊነታቸው አይደለም፡፡ አይሲስኮ ዜግነት የለውም፡፡ ዐረቦች፣ አውሮፓውያን፣ አፍሪካውያን እስያውያን የተቀላቀሉትአሸባሪና አሰቃቂ ድርጅትና አስተሳሰብ ነው፡፡ እንዲያውም ባለፈው ሰሞን ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከእንግሊዝ ወደ አይሲስ ለመግባትያደረጉትን ጥረት በመገናኛ ብዙኃን […]
