የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር የሃገሪቱን ካቢኔ ካገዱ በኋላ ዋና ዋና የመንግሥት ተቋማት አካባቢ ጥበቃው ተጠናክሯል ። ከፕሬዝዳንቱ እርምጃ በኋላ ህዝቡ እንዲረጋጋ በራድዮ ጥሪ ተላልፏል ። ከሥልጣን ከተወገዱት ባለሥልጣናት መካከል ተሰሚነት ያላቸው ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቼርና የገዥው የሱዳን ህዝቦች ነፃ አውጭ ንቅናቄ በእንግሊዘኛው ምህፃር SPLM ዋና ፀሃፊ ፓጋን አሙም ይገኙበታል ። የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ […]
