በደቡብ ኢትዮጵያ ሸካ ዞን የሚገኙ የቴፒ ወጣቶች በህወሓት አገዛዝ የሚደርስባቸው በደል አንገሽግሿቸው ራሳቸውን አደራጅተው በአገዛዙ ላይ እርምጃ መውሰድ ከጀመሩ በርካታ ወራት ተቆጥረዋል። እነዚህ ወጣቶች ግንቦት 27 ቀን 2007 ዓ.ም. በአካባቢያቸው የሚገኝን አንድ የፓሊስ ጣቢያ ወረው እስረኞችን ማስፈታታቸው በመላው ኢትዮጵያ እንዲታወቁ ምክንያት ሆኗል፤ የአገዛዙ ሚዲያም ድርጊቱ መፈፀሙ በተዘዋዋሪም ቢሆን አምኗል። ለፍትህ፣ ለነፃነት፣ ለዲሞክራሲ፣ ለእኩልነት እና ለአገር […]
