እራሱን ጽናት እያለ በሚጠራው ጀሌ ላይ በቀረበው ጽሁፍና ማስተባበያ ለቀረበበት «ዘረፋ» ግልጽ የሆነ ማስረጃ ! ድምጻችን ይሰማን ለሁለት በመስንጠቅ የህዝበ ሙስሊሙን አንድነት ለመናድ ሀወሃት/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ እንቅልፍ አጥቶ ማደርየጀመረው ዛሬ እንዳልሆነ የታወቃል ።ህወሃት/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የሃይማኖት ነጻነት ትግሉ በተጀመረ ማግስት መፍትሄ አፈላላጊኮሚቴ አባላትን ዘብጥያ በማውረድ ለይስሙላ ያፀደቀውን ህገመንግስታዊ መብት በመተላለፍ የህዝቦችን መብት በጠመንጃአፈሙዝ ጨፍልቆ ለጸሎት አደባባይ የወጣውን አዛውንት ሴት ወጣት ሳይል ያገኘውን ሁሉ በደም በጨቀዩ ልዩ ኮማንዶዎቹበጥየት ረሽኗል ፤ ከሞት የተረፈውን በቆመጥ ደብድቦ በክሚዎን በማጋዝ ወዳልታወቀ ስፍራ ወስዶ አስሮ በማሰቃየት ላይይገኛል። ታዲያ ይህን ሁሉ ግፍና ስቆቃ የተቀበለው ኢትዮጵያዊ ሙስሊም አንድነቱን ጠብቆ ሰላማዊ ተቃውሞውን የበለጠበማጠናከር ሳይገድል እየሞተ ለአምባ ገነኖች የአላማ ጽናቱን በተግባር አሳይቷል በማሳየትም ላይ ይገኛል። ይህ የህዘበሙስሊሙ አንድነትና ለሃይማኖቱ ነጻነት ያለው ቁርጠኝነት እንቀልፍ የነሳው ሀወሃት መራሹ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስረአት የበግልምድ ለብሶ ውሎና አድሩን ህዝበ ሙስሊሙ ጉያ ውስጥ በማድርግ በማህበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸውን ዑለማዎችየሃገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች በኃይል አሊያም በግዜያዊ ጥቅም በማግባባት ለዚህ እርኩስ ሴጣናዊ ተግባሩማስፈፀሚያ ግበአት እንዲሆኑ ለማድረግ ሃገር ውስጥና በውጩ አለም እየዞረ ያልፈነቀለው ድንጋይ ያልቦጠጠው ተራራየለም። ለአብነት ያህል የፖለቲከኛውን ጁሃር መሃመድ አሳዛኝ ታሪክ ወደ ጎን ትተን በእስቷዝ ሃስን ታጁ ስም አዲስ አበባ ላይቀደም ሲል የተበተነውን ከፋፋይ የሆነ ባለ10 ገጽ ጽሁፍ ማስታወስ ከበቂም በላይ በቂ ማስረጃ ነው ።በእስቷዝ ሃስን ታጁጽሁፉ ላይ «ሰላማዊ ትግሉን የተቀላቀሉ ወጣቶች አላዋቂ፣ስሜተኛ፣ጃሂል አድርጎ ለማቅረብ ከተደረገው ጥረት ባሻገርየተቃውሞ አካሔድ ሌላ መንገድ ቢፈለግለት በሚል አሳፍሪ አቋም በተለይም የጁሙዓ ተቃውሞዎች መቋረጥእንዳለባቸውና ኮሚቴዎቻችን ይቅርታ ጥይቀው እንዲወጡ » ህወሃት/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ህዝበ ሙስሊሙን ተመስሎበዑለማዎቻችን አንደበት ያሻውን መልዕክት በድፈረት ይስተላለፈበት ያ ! ፈታኝ የትግል ዘመን የቅርብ ግዜ ትዝታ ነው ዛሬ ከዚህ አፍራሽ ተዕልኮ ባልተለየ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ካድሬዎች አይናቸውን በጨው ታጥበው ሳውዲ አረቢያ ጅዳ ና ሪያድከተማ ውስጥ ብዙሃኑ ተመስለው ሊያሰሙን በሞከሩት ጩኋት በአካባቢው ያሉትን ስመጥር የሃይማኖት አባቶችና እሩቅያሉትን የህዝበ ሙስሊሙን ነጻ ሚዲያዎች ቀልብ አሳስተው ለዚህ መስሪ ተግባራቸው ግበአት በማድረግ በህዝበ ሙስሊሙአንድንተ ላይ አደጋ ከመጋረጥ አልፈው በአቋራጭ የግል ኑሮቸውን ለማደርጀት ሲያደርጉ የነበረው ጥረት በሃገር ሽማግሌናበኃይማኖት አባቶች ተጋልጦል ዝርዝር መረጃውን ሊንኩን ይጫኑ ኢንጂነር መሃመድ አባስ ከሪያድ ሳውዲ አረቢያ posted by Aseged TameneFiled under: NEWS Tagged: Addis Ababa, Addis Ababa University, Africa, African Commission on Human and Peoples' Rights, EPRDF
