የአዲስ አበባ ፖሊስ መምህር ግርማ ወንድሙን በቁጥጥር ስር አዋለ። የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ምንጮች መምህር ግርማ ዛሬ በፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ተናግረዋል። መምህር ግርማ በተለያዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት በማስተማርና በማጥመቅ ሲያገለግሉ የነበሩ ናቸው። ይሁን እንጂ መምህሩ በማጥመቅ እና በማስተማር በሃገር ውስጥም ይሁን በውጭ ሃገራት ቤተክርስቲያኒቱን ወክለው እንዳያገለግሉ እውቅና መነፈጋቸውን ፋና […]
