ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ በዝዋይ ማረሚያ ቤት ቆይታው ንጹህ የመጠጥ ውሃ ማግኘት ባለመቻሉ ለከፍተኛ የኩላሊት ህመም ተዳርጓል፡፡የተደረገለት የኤክስሬይ ምርመራም በግራ ኩላሊቱ የአሸዋ ክምችት መታየቱን ባለሞያዎች ተናግረዋል፡፡የማረሚያ ቤቱ ክሊኒክ ባለሞያዎች ለውብሸት ህመም የሚሆን መድሃኒት ማግኘት ባለመቻላቸው ፓራሲታሞል ሲሰጡት ከርመዋል፡፡ህመሙ ጠንቶ ወደ አዲስ አበባ ቢያመራም ጋዜጠኛውን የተረከቡት የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሃላፊዎች ከክሊኒካቸው ውጪ ገንዘብ ከፍሎ እንኳ በግል ሆስፒታል […]
