ሰማያዊ ፓርቲ ኢትዮጵያዊያን ህዝባዊ መንግስት መመስረት እና የሐገር ሉዓላዊነትን ማስጠበቅ የእያንዳንዱ ዜጋ ኃላፊነት መሆኑን ተገንዝበው ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳሰበ፡፡ ፓርቲው ‹‹ሕዝባዊ መንግስት መመስረትና የሐገር ሉዓላዊነት መጠበቅ የእያንዳንዱ ዜጋ ኃላፊነት ነው›› በሚል ዛሬ ታህሳስ 20/2008 ዓ.ም በጽ/ቤቱ በሰጠው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው፣ ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ በከፋ የፖለቲካ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ምስቅልቅል ውስጥ ትገኛለች፡፡ መግለጫውን የሰጡት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር […]
