በመርሳቢት ካውንቲ ሞያሌ ከተማ የኢትዮጵያ ወታደሮች ሁለት ኬንያዊያንን አፍነው መውሰዳቸው ተነገረ፡፡ የግዛቱ ኮሚሽነር ሞፋት ካንጊ 100 የሚደርሱ የኢትዮጵያ ወታደሮች በሞያሌ ቦሪ መንደር ዘልቀው በመግባት ሁለቱን ሲቪል ኬንያዊያንን መውሰዳቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ኮሚሽነሩ የተወሰዱትን ኬንያዊያን ለማስመለስ እየሰሩ መሆናቸውን በመግለጽ ሁለት መሳሪያዎችን የኢትዮጵያ ወታደሮች ሰርቀው መውሰዳቸውን አስረድተዋል፡፡ ‹‹ጥቃቱን ያደረሱበትን ምክንያት ለማወቅ እየጣርን ነው፡፡ሰዎቹ የኢትዮጵያ የደህንነት ኤጀንሲዎች አባላት ናቸው፡፡የጸጥታውን ጉዳይ […]
