የኬንያው ፕሬዘዳንት ዛሬ ባደረጉት ንግግር አልሻባብ በሶማሊያ የሚገኘውን የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ጦር ካምፕ በማጥቃቱ ኬንያዊያን ወታደሮች መገደላቸውን ገልጸዋል፡፡ፕሬዘዳንቱ ምን ያህል ወታደሮች በጥቃቱ እንደተገደሉ ባይገልጹም የአልሻባብ ቃል አቀባይ ለቢቢሲ በሰጠው ቃል 63 የኬንያ ወታደሮች መገደላቸውን ጠቅሷል፡፡ ፕሬዘዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ሁኔታው በጣም አሳዛኝ እንደነበር በማብራራት ‹‹የተወሰኑት ጀግኖቻችን ዩኒፎርማቸውን እንደለበሱ ትልቁን መስዋዕትነት መክፈላቸውን ስገልጽ ሀዘን ይሰማኛል፡፡ይህንን አጋጣሚ […]
