የስልጣን ጥመኝነት የወለደዉ የፀረሽብር አዋጅ የፀረሽብር አዋጁንና እየተተገበረ ያለበትን መንገድ ባሰብኩ ቁጥር ወደ አዕምሮዬ የሚመላለሱ በርካታ ጥያቄዎች አሉ፡፡ ከነዚህ መሀከል አዋጁ ለምን ሰብአዊ መብትን የሚጥሱ አንቀጾች ኖሩት/ ከሽብር ጋር ምንም አይነት ንክኪ የሌለን ንጹሀን ሰዎችስ በአዋጁ መሰረት እየተባለ ለምን ይፈረድብናል የሚሉት ይገኙበታል፡፡ እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ አዋጁ የወጣበትን ምክንያት መመርመር ግድ ይላልና ይህንኑ አደረስኩ፡፡ የፀረሽብር አዋጁ […]
