ዜና ከደቡብ ኢትዮጵያ በሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ የከተማ ታክሲዎችን ጨምሮ የህዝብ ማመላለሺያ ተሽከርካሪዎች ከትላንት ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ አድርገዋል። መንግስት በአሽከርካሪዎች ላይ ያወጣው አዲስ መመሪያን ተከትሎ በተነሳ ቁጣ አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች የስራ ማቆም አድማ መምታቸውን ለኢሳት ከአከባቢው የደረሰው መረጃ አመልክቷል። ከትላንት ጀምሮ ምንም አይነት የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከሆሳዕና መግባትም መውጣትም እንዳልቻለ በአድማው የተሳተፈ አንድ አሽከርካሪ ገልጿል። […]
