ወጣቱ ደራሲና ገጣሚ በዕውቀቱ ስዩም “ከዐሜን ባሻገር” የተሰኘ መጽሐፉን እሁድ ጥር 22 ቀን 2008 ዓ.ም በሐዋርድ ዩኒቨርስቲ ብላክ በርን ሴንተር አስመርቋል። ከምርቃት ዝግጁቱ በኋላ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጠው ቃለምልልስ፤ ስለመጽሐፉ ርእስ ስያሜ ተጥይቆ፤ “አሜን ብለን ስንቀበላቸው የቆየናቸው የታሪክ፣ አልፎ አልፎም የፖለቲካ አስተያየቶች፣ ስለ አኗኗራችን በተቋሞች፣በትምሕርት ቤት፣ በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ወይም ደግሞ መንግሥታዊ ባልሆኑ በተለያዩ ተቋሞች አማካኝነት […]
