በኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር መነሻነት የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ተከትሎ ለእስር የተዳረጉ በርካታ ሰዎች በቃሊቲና ሌሎች እስር ቤቶች ስቃይ እየተፈጸመባቸው መሆኑን የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብት ሊግ አስታወቀ። እነዚሁ በጨለማ ክፍል ታስረው የሚገኙ እስረኞች በጸጥታ ሃይሎች ለሰዓታት የቆየ ድብደባና እንግልት እየተፈጸመባቸው እንደሚገኝ ሊጉ የተለያዩ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ይፋ አድርጓል። በዚሁ የቃሊቲ እስር ቤት ከድር ዝናቡ፣ […]
