በኢትዮጵያ በፕሬስ ነጻነት ላይ የሚደረገው ገደብና የጸረ ሽብር ሕጉን በመጠቀም መንግስት በጋዜጠኞች፥በመብት ተሟጋቾችና በተቃዋሚዎች ላይ የሚያደርገው ጫና የሚያሳስባት መሆኑን ዩናይትድ ስቴትስ አስታወቀች። በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞው የጋምቤላ አስተዳዳሪ እንዲለቀቁና በኢትዮጵያ የዜጎች መሠረታዊ መብቶችእንዲከበሩ በመጠየቅ አምስት የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት ከትላንት በስቲያ ለፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማየጻፉትን ደብዳቤ ተንተርሶ ለቀረቡ ጥያቄዎች በሰጠው ምላሽ ነው፤ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ […]
