ይሄይስ አእምሮ ወቅቱ በኦርቶዶክሳውያንና በኢትዮጵያውያን ካቶሊኮች ዘንድ የፍልሰታ ለማርያም የፆምና የሱባኤ ጊዜ ነው፡፡ በዚህ ለየት ባለ የሱባኤ ወቅት ለምንገኝ ወገኖች ፈጣሪ የልባችንን መሻት ተረድቶ የዘመናት ህልማችንን በቅርብ እውን ያድርግልን፤ የሚሳነው ነገር የለምና፡፡ ጸሎት ምህላችንን ሰምቶ ከነዚህ ሽል መንጣሪዎች፣ ከነዚህ የሰው ግርድ እና አመሳሶ አውጪዎች ይገላግለን፡፡ የእስላም የክርስቲያኑን ዕንባ ተመልክቶ ከነዚህ ሰው በላዎች ነጻ የምንወጣበትን መንገድ […]
