ዩጋንዳ በነጭ አባይ ላይ የምትገነባውን 600 ሜጋ ዋት የኤሌከትሪክ ኃይል የሚያመነጨውን የግድብ ግንባታ ስራ መጀመሯን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሰቬኒ ገለፁ፡፡ ዩጋንዳ በ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር በነጭ አባይ ላይ የምትገነባው የካሩማ ግድብ በቻይናው ሲንዮ ሀይድሮ ኮርፖሬሽን ይገነባል፡፡ የዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሰቬኒ ለዚህ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ስራ የሚያስፈልገውን የገንዘብ ወጭ እና ቴክኒካዊ ድጋፍ በቻይና በኩል እንደሚሸፈን ገልጸዋል፡፡ […]
