የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሰብዓዊ መብት ካውንስል በኢትዮጵያ ሰሞኑን በተካሄዱት ሕዝባዊ ተቃውሞዎች የሰብዓዊ መብት አያያዝን ለማጣራት የጠየቀውን ፈቃድ መንግሥት ውድቅ አደረገ፡፡ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች በርካታ አካባቢዎች በተነሱት ተቃውሞዎች የሟቾችና የተጐጂዎች ቁጥጥርን አስመልክቶ በመንግሥት እየወጣ ያለው ሪፖርት ተዓማኒነትን በመጠራጠር ነው፣ የተመድ ሰብዓዊ መብት ካውንስል ጥያቄውን ያቀረበው፡፡ በሰብዓዊ መብት የተመድ ከፍተኛ ኮሚሽነር የሆኑት ዚያድ ራድ አል ሁሴን […]
