ውድ የአገራችን ጀግኖች ለነጻነታችሁ የምታደርጉት ተጋድሎ ወደር የማይገኝለት መሆኑን ስንነግራችሁ በኩራት ነው። ይህን ተጋድሎአችሁን በጠመንጃ ሃይል ለማፈን የወያኔ አገዛዝ የሚወስደው ፋሽስታዊ እርምጃ አልበቃ ብሎት፣ አሁን ደግሞ የስነ ልቦና ዘመቻ ከፍቶባችኋል። አባቶቻችሁን ፣ እናቶቻችሁን፣ ወንድሞቻችሁንና እህቶቻችሁን በየመድረኩ እየጠራ እናንተን እንዲያወግዙ እየስገደደ ነው። አድሎአዊነትና ኢፍትሃዊነት አንገሽግሾአችሁ ያቀጣጠላችሁትን የነጻነት ትግል ለማራከስ፣ ታሪካችሁን ለማቆሸሽ ላይና ታች እያለ ነው። የእናንተ […]
