ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም የተለያዩ ጥያቄዎች የተነሱበት ሰላማዊ ሰልፍ አድርጎ ነበር፡፡ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ስለሙስሊሙ የሐይማኖት ጥያቄ፣የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችና የፖለቲካ እስረኞች ባፋጣኝ እንዲፈቱ፣ስለኑሮ ውድነት ወዘተ ነበር በሰልፉ ላይ የተስተጋባው፡፡ በሰልፉ ማብቂያ ላይ እንደተነገረው እነነዚህ ጉዳዮች በ3 ወር ጊዜ ውስጥ የማይመለሱ ከሆነ እንደገና የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚጠሩ በእለቱ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ተናገረው ነበር፡፡ […]
