ሰው ገብቶ እንዲጠይቀው ተፈቅዶለታል ‹‹ስላደረጋችኹልኝ እና ስለምታደርጉልኝ ኹሉ አመሰግናለሁ›› ብሏል ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ቃሊቲ የሚገኘው እስር ቤት ከገባ ከዐሥራ ስምንት ወራት በላይ አስቆጥሯል፡፡ ለዚህን ያህል ጊዜም ከባለቤቱ ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል እና ከልጁ ናፍቆት በስተቀር አንድም ሰው ገብቶ እንዲጠይቀው አልተፈቀደለትም ወይም በወዳጅ ዘመዶቹ የመጠየቅ መብቱ ተነፍጎ ነበር፡፡ ከቀናት በፊት ግን ይህ መብቱ ተከብሮለት ሰዎች ገብተው እንዲጠይቁት […]
