በትናንትናው እለት የነጻነት ትግል ተሳታፊ ናችሁ የተባሉ እስረኞችን ወቅን ከተባለች ስፍራ ወደ ዳባት ከተማ ይዘው በመጓዝ ላይ በነበሩ ፖሊሶች ላይ ሳይታሰብ ድንገት በተከፈተ ተኩስ ሁለት ፖሊሶች ሲገደሉ ሁለት እሰረኞችም በተመሳሳይ ሁኔታ ሰማዕታት ሆነዋል። ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቀ ከፖሊስምሆነ ከእስረኞቹም የቆሰሉ መሆኑ ታውቋል። የሟቾቹ አስከሬን በዳባት ፖሊስ ጣቢያ በአሁኑ ስአት የሚገኝ ሲሆን ። ዳባት ከተማ ከፍተኛ አለመረጋጋት […]
