በደቡብ ወሎ ዞን ኩታበር ወረዳ በአንድ ግቢ ውስጥ የሚገኙት የወረዳው ምክር ቤት፣ ማዘጋጃ ቤትና የብአዴን ጽ/ቤቶች የእሳት ቃጠሎ ደርሶባቸዋል፡፡ መጋቢት 26 ለ27 ሌሊት 2009 ዓ.ም ሦስቱም በአንድ ግቢ ውስጥ ያሉ መሥሪያ ቤቶች እንዲቃጠሉ መደረጋቸውን የተናገሩት ምንጮች ሁሉም በጋራ የሚጠቀሙበት መዝገብ ቤቱ ሙሉ በሙሉ መውደሙን አሰምተውናል፡፡ ይህን ተከትሎ በኩታበር ከፍተኛ ውጥረትና መደናገጥ የተፈጠረ ሲሆን ከጉዳዩ ጋር […]
