ኦጋዴን ኒውስ ኤጀንሲ እንደዘገበው ከሁለት ቀናት በፊት በመከላከያ ሰራዊት በሚደገፈው የሶማሊ ልዩ ሃይልና በኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት መካከል በደጋሃቡር አውራጃ፣ በብርቆት ወረዳ ልዩ ስሙ ሊዲለይ በሚባል ስፍራ ላይ በተደረገ ውጊያ 3 አዛዦችን ጨምሮ 17 ወታደሮች መገደላቸውን የአይን እማኞችን ጠቅሶ ዘግቧል። 21 ቁስለኛ ወታደሮች ደግሞ በአየር ወደ ጅግጅጋ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የአይን እማኞች እንደገለጹለት የዜና ድርጅቱ አስታውቋል። […]
