የህወሓት አገዛዝን በመሰለ አፋኝ ሥርዓት የሚገኝ ሕዝብ ለተቃውሞ መግለጫነት የሚያገለግሉ አጋጣሚዎችን ሁሉ መጠቀሙ ብልህነት ነው። ብሔራዊ፣ ባህላዊና የሀይማኖት በዓላት፤ የሙዚቃ ድግሶች፤ የስፓርት ሜዳዎች፤ ትምህርት ቤቶችና ገበያዎች ለተቃውሞ መነሻነት ምቹ ናቸው። እነዚህን ሁሉ በአግባቡ መጠቀም ለሁለገብ ትግል ውጤታማነትና ሕዝብን ለማነቃቃት ከፍተኛ አስተዋጽዖ አላቸው። በተለይ የእግር ኳስ ግጥሚያዎች በርካታ ሕዝብ በጠባብ ቦታ የሚሰበሰብባቸው በመሆኑ፤ አብዛኛው ተመልካችም በእድሜ […]
