በህወሃት የበላይነት የሚመራው አገዛዝ እየገጠመው ያለውን ተቃውሞ ለመቆጣጠር ደፋ ቀና እያሉ ካሉ ከፍተኛ አመራሮች መካከል በረከት ስሞኦንና አዲሱ ለገሠ የብአዴንን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ለመከታተል ባህር ዳር ከተማ መክተማቸውን ከውስጥ አዋቂ ምንጮች የደረሰው መረጃ አመለከተ። የብአዴን የቀድሞ አመራሮች የነበሩ በረከት ስሞኦንና አዲሱ ለገሠ አለቃቸው መለስ ዜናዊ በህይወት በነበረበት የመጨረሻዎቹ አመታት መተካካት በሚለው የወያኔ ፖሊሲ የክልል ሥልጣናቸውን ለአዳዲስ የፓርቲው አባላት አስረክበው […]
