ቃሊቲ እስር ቤት በከተማ ውስጥ ያለ አነስተኛ የማይሰኝ ከተማ ከሆነ ከራረመ፡፡የታሰረ ሰው ለመጠየቅ ጎራ ካሉ በዚያ ለአመታት ከእይታዎ የራቀን ሰው ታስሮ ወይም የታሰረ ሊጠይቅ መጥቶ ሊያገኙት ይችላሉ፡፡ወህኒ ቤቱ ስንት ሺህ ካሬ ላይ እንዳረፈ መረጃ ባላጠናክርም ‹‹የከተማ ውስጥ ከተማ››የሚለው ስያሜ ቢያንሰው እንጂ አይበዛበትም፡፡ የእስር ቤቱ ስፋት ሁሉን ውጦ ጸጥ ለማለት አስችሎታል፡፡የሃይማኖት መምህራን፣የህክምና ባለሞያዎች፣የቀድሞ መንግስት ሃላፊዎች፣የጦር ጀነራሎች፣ካድሬዎች፣አክቲቪስቶች፣ጋዜጠኞች፣ደረቅ […]
