(ዘ-ሐበሻ) ከሳዑዲ አረቢያ 13 ግዛቶች ውስጥ በሰው ብዛት 7ኛ እንደሆነች በሚነገርላት አል ቃሲም ከተማ ስደተኞችን ማፈስ ተጀመረ። ከትናንት ጀምሮ ፖሊስ በየቤቱ እየሰበረ በመግባት ስደተኞችን እያፈሰ መሆኑን ከአካባቢው የዓይን እማኞች ለዘ-ሐበሻ በላኩት መረጃ ዘገበዋል። ከዚህ ቀደም በሪያድና በመካ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሞት፣ ለድብደባ፣ ለዝርፊያና ለአስገድዶ መደፈር ያበቃው ስደተኞችን የማባረሩ ተግባር ወደ አልቃሲም ከተማ ተሸጋግሮ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ […]
