ባለፈው እሑድ ኅዳር 15 ቀን 2006 ዓ.ም. በጃንሜዳ በተካሄደው 13ኛው ታላቁ ሩጫ ላይ እንደሚሳተፉ አስታውቀው የነበሩ የውጭ አገር አርቲስቶች የአሸባሪዎች ጥቃት ሊሰነዘር ይችላል በሚል ሥጋት ሳይሳተፉ መቅረታቸው ተሰማ፡፡ የአየርላንድ መገናኛ አውታር የሆነው አይሪሽ ኢንዲፔንደንት በድረ ገጹ እንዳስታወቀው፣ በአሥር ኪሎ ሜትሩ የታላቁ ሩጫ ላይ በመሳተፍ ለበጎ አድራጎት ተቋም ገቢ ማሰባቢያ ይሆን ዘንድ እንደሚሮጡ ይጠበቁ ከነበሩት መካከል […]
