ተቋማቱ በኤጀንሲው የተሠራውን ‹‹ዳጉ ሜይል›› መጠቀም ይገደዳሉ የመረጃ ደኅንነት ኤጀንሲ በቅርቡ በፀደቀው አዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ቁልፍ የመንግሥት ተቋማት የኤሌክትሮኒክስ መረጃዎችና ኢንተርኔትን መሠረት ያደረጉ የመረጃ ልውውጦች ከኢንተርኔት ‹‹ሃከሮች›› (በርባሪዎች) ለመከላከል የሚያስችል ቴክኖሎጂ ይፋ ሊያደርግ ነው፡፡ ቁልፍ የሚባሉ የመንግሥት ተቋማት እንደ ጂ-ሜይል (Gmail) ያሉ የኢንተርኔት መልዕክት ማስተላለፊያዎችን እንዳይጠቀሙ ሊገደዱ ነው፡፡ ኤጀንሲው በቅርቡ ተግባራዊ ለማድረግ እያበለፀገ የሚገኘው […]
