ጥዋት 3 ሰአት አዲስ አበባ የለቀቀዉ አይሮፕላን 7.30 ጆበርግ ገባ፡፡ከዚህ በሁዋላ ነዉ አስደንጋጭ ወሬዎች መሳመት የጀመሩት…3ት ጋዜጠኖች ከቡድኑ በፊት አስቀድመዉ ሀሙስ ጆበርግ ደረሱ፡፡እናም የወረቀት ቪዛ (አክሪዲቴሽን) ነበር የያዙት..የደቡብ አፍሪካ ሚግሬሽን ይህን የካፍን ይለፍ አልቀበልም…በህገወጥ መንገድ ነዉ የገባችሁት በሚል ተያዙ፡፡ኢብራሂም ሻፊ…ይሳቅ በላይ እና ፍስሀ ይድነቀቸዉ ከሀሙስ ጀምረዉ እስከዛሬ ምሽት ድረስ ታስረዉ ቆዩ፤የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት እና የደቡብ አፍሪካ […]
