ለ15 አመት በአሜሪካ ኖሯል። ስሜን አትግለፅ ስላለኝ..« አዘነ» እያለኩ እቀጥላለሁ። አዘነን በአንድ ጓደኛዬ አማካይነት ተዋወቅን። የደረሰበትን በደል ሲተርክልኝ…በሃዘን ስሜት ተውጦ ነው። ታሪኩ እንዲህ ነው፤..አዘነ ብቻውን ነበር የሚኖረው። በአጋጣሚ በለጠ የተባለ (ስሙ ቀይሬዋለሁ) ሰው ጋር ይቀራረቡና ጓደኝነት ይመሰርታሉ። በለጠ አሜሪካ ከመጣ ሶስት አመት ሆኖታል። « ለምን ትዳር አትመሰርትም? እስከመቼ ብቻህን ትኖራለህ?..» በማለት በለጠ ደጋግሞ አዘነን ይጠይቀዋል። […]
