ሙስና እንደአስተሳስብ በሀገራችን የቆየ ቢሆንም ባለፉት ዐስር ዐመታት ግን በብርሀን ፍጥነት አድጎ ባለስልጣኖቻችን፣ ነጋዴዎቻችን፣ ባለሀብቶች ሙስና መስራት ሳይሆን አለመስራቱ እንደነውር እየቆጠሩት ነው፡፡ ባሁኑ ሰዐት ስሙ ራሱ ተቀይሮ “ቢዝነስ” ተብሎ የየዕለት ገጠመኝ፣ የተለመደ የቢሮክራሲው አካል ሆኗል፡፡ ለዛሬ በባለስልጣኖች(የታችም የላይም) ያለውን ሙስና ብናይ፤ ባሁን ሰዐት ሶስት ዐይነት ሙሰኞች አሉ፡፡ 1. ትንሽ እየሰሩ የሚሰርቁ፡፡ በተሰማሩበት ስራ በተወሰነ መልኩም […]
